ራዕይ ማግኘት ድፍረትን ማግኘት

Share This Post

እግዚአብሔር ለተለየ አላማ ፈጥሮሀል፡፡ ራዕይ ለዚህ ዓላማ እንድትለቀቅ እግዚአብሔር የሚጠቀምበት መሳሪያ ነው፡፡

መፅሐፍ ቅዱስ በመዝ 139፤13-14 ላይ

‹‹አቤቱ አንተ ኩላሊቴን ፈጥረሃልና በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል፡፡ ግሩም እና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሪያለሁና አመሰግናለሁ ሥራህ ድንቅ ነው፡፡ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች፡፡››

ራዕይ የውስጥ ስሜትን የሚያንፀባርቅ እና አዕምሮን፣ ስጋንና ነፍስን የሚያነሳሳ ሸክምን የሚፈጥር የወደፊት ምስል ነው፡፡ ፈታኙም ነገር ይህንን ራዕይ ማግኘት ለመኖር የሚያስፈልገውን ድፍረት ማግኘት ነው፡፡

ስለ ወደፊትህ ምን ታልማለህ? በአምሮህ ልትሰለው ትችላለህ? ለአንድ አንዶች ይህ ምስል ቶሎ ይመጣል፡፡ ለአብዛኞች ሰዎች ግን ይህንን ለማግኘት ጉዞን ማለፍ አለባቸው፡፡

እስኪ በወረቀት ላይ ወደፊት ልትሆን የምትፈልገውን ነገር ገልፀህ ፃፍ፡፡ ቃላትን ወይም ምስሎችን መጠቀም ትችላለህ፡፡ ከልብህ እንዲፈልቅ ፍቀድ፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ ብዙ ረቂቆችን ፍቀድ ለህይወትህ የእግዚአብሔርን ራዕይ ለማወቅ ይህ የመጀመሪያ እርምጃ ነው፡፡ እና እንድንረዳህ ከፈለግህ ፃፉልን ራዕይህን አጋራን ወይም እኛን ጠይቀን፡፡

እግዚአብሔር ለህይወትህ ያለውን አላማ እንዲገልፅልህ ለመጠየቅ ድፈር፡፡

Subscribe To Our Newsletter

Get updates and learn from the best

More To Read